Fana: At a Speed of Life!

የመንገድ ትራፊክ አደጋን ተከላክሎ በማሽከርከር ረገድ ሴት አሽከርካሪዎች ያላቸው ሚና የላቀ እንደሆነ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመንገድ ትራፊክ አደጋን ተከላክሎ በማሽከርከር ረገድ ሴት አሽከርካሪዎች ያላቸው ሚና የላቀ እንደሆነ ተገለፀ።

የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ሴት የብዙሃን ትራንስፖርት አሸከርካሪዎች፣ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሴት የስራ ኃላፊዎች አደጋን ተከላክሎ በማሽከረከር ዙሪያ እየተሰጠ ያለውን ስልጠና አስጀምረዋል።

በዚህ ወቅትም ሴት አሽከርካሪዎች ከብዛት አንጻር በትራንስፖርት ዘርፍ ያላቸው ድርሻ ወሳኝ ቢሆንም ያሉት አሽከርካሪዎች ግን አደጋን ባለማድረስ፣ በመከላከል እና ህግን በማስከበር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ይህንንም ማስፋት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል::

ስልጠናው የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከተያዘው ሀገራዊ የንቅናቄ መርሃ ግብር አንዱ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሴቶች በዘርፉ ካላቸው ሙያዊ አስተዋጽኦ በተጨማሪነት እንደ ቤተሰብ ሃላፊም በልጆች ላይ ግንዛቤ ከመፍጠር አንጻር አወንታዊ ተጽዕኖን ለማሳደር እድሉ ስላላቸው ይህ አቅም መገንቢያ ስልጠና ወሳኝ ነው ሲሉ መግለፃቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሚኒስትሯ ከስልጠናው የሚገኘውን ግንዛቤ በአግባቡ በመተግበር የትራፊክ አደጋ እንዲቀንስ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለተሳታፊዎቹ ጥሪ አቅርበዋል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.