Fana: At a Speed of Life!

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለፈው በጀት አመት ከታክስ በፊት 55 ነጥብ 55 ቢሊየን ብር አተረፉ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር ያሉ 21 የልማት ድርጅቶች በ2012 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 55 ነጥብ 55 ቢሊየን ብር አተረፉ፡፡

ትርፉ በበጀት ዓመቱ ከተሰጠ የ300 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ምርትና አገልግሎት ሽያጭ የተገኘ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረመስቀል ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም 8 ነጥብ 67 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ምርትና አገልግሎታቸውን በውጭ ምንዛሪ ከሸጡ ድርጅቶች መገኘቱንም ነው የተናገሩት፡፡

በተያዘው በጀት አመትም የልማት ድርጅቶቹ 376 ነጥብ 66 ቢሊየን ብር የምርትና አገልግሎት ሽያጭ ለማከናወንና ከታክስ በፊት 73 ነጥብ 81 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዷልም ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.