Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ኃይል በምእራብ ትግራይ ግንባር እየወሰደ ባለው ህግን የማስከበር እርምጃ እስካሁን 550 የፅንፈኛው ታጥቂ ቡድን አባላት ተደምስሰዋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ኃይል በምእራብ ትግራይ ግንባር እየወሰደ ባለው ህግን የማስከበር እርምጃ እስካሁን 550 የፅንፈኛው ታጥቂ ቡድን አባላት መደምሰሳቸው ተገለፀ።
በተጨማሪም በዛሬው እለት ብቻ 29 የልዩ ሃይል እና ሚኒሻ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነው የተገለፀው።
የፅንፈኛው ታጣቂ ቡድን በዚህ በግንባር ከፍተኛ ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑም ተነግሯል።
እስካሁንም 115 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 11 መትረየስ፣ 2 ድሽቃ፣ 8 አር ፒጂ ከባድ መሳሪያ፣ 152 የእጅ ቦንብ፤ 2 ስናይፕር፣ 4 ኤም-14 ጦር መሳሪያ፣ 2 ኢንኮም ሬድዬ በቁጥጥር ስር ውሏል።
በተጨማሪም 21 ሺህ 650 የክላሽ ጥይት፣ 14 ሸህ 730 የመትረየስ ጥይት፣ 1 የጦር ሜዳ መነፅር፣ 64 የጦር ሜዳ ቀበቶ፣ 6 የአር ፒ ጂ ቅንቡላ፣ 90 የክላሽ መጋዘን እና 10 የመትረየስ ዝናር በቁጥጥር ስር ውሏል።
እንዲሁም ከሰሜን እዝ 5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ተዘርፈው የነበሩ 5 ታንኮች ሲመለሱ አንዱ ባለበት እንዲወድም መደረገጉ ታውቋል።
የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል በላይ ስዩም፥ ህግን የማስከበር ዘመቻው በስፋት እና በድል ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።
የሰራዊቱ ተልእኮን የመፈፀም ብቃት ከየትኛውም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት ዋና አዛዡ፥ ስራዊቱ ዳንሻ ትርካን ዲቪዥን ባእኸር ራውያንን እና የሁመራ ከተሞችን መቆጣጠሩንም ተናግረዋል።
በዳዊት መስፍን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.