Fana: At a Speed of Life!

የመውሊድ በዓል በሆሳዕና ከተማ በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 496 ኛው የመውሊድ በዓል በሆሳዕና ከተማ በታላቁ ፈቲህና ኑር መስጅዶች የዕምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ተከበረ፡፡
አከባበሩ የነቢዩን መልካም ምግባራትን በሚያወድሱና በሚያንጸባርቁ ነሺዳዎችና መንዙማዎች ነው ታጅቦ የተከበረው፡፡
የፈቲህ መስጂድ ኢማም ሼህ ሙክታር ሀሰን ሰኢድ እንዳሉት÷ መውሊድ ማለት ነቢዩ መሐመድ (ሶሎላሁ አለይህ ወሰለም) የተወለዱበት ቀን ሲሆን÷ ይህም ቀን እሳቸው በምድር ላይ ሳሉ የሰሯቸውን መልካምና በጎ ተግባራትን በማሰብ የሚከበር ነው።
የኑር መስጅድ ኡስታዝ ኢስማኤል ሸምሰዲን በበኩላቸው÷ የመውሊድ በዓል የሚከበርበት የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት ቀን በምዕመናን ዘንድ ልዩ የደስታ ስሜት የሚፈጥርና ሰዎች አንድነታቸውን ይበልጥ አጠናክረውና አጉልተው የሚያሳዩበት ስለመሆኑ ገልፀዋል።
ምዕመኑ በዓሉን ሲያከብር የመረዳዳትና የመተሳሰብ ዕሴትን ማጎልበትና ለሀገሩ ሰላም መረጋገጥ የበኩሉን መወጣት እንዳለበትም አሳስበዋል።
የበዓሉ ተሳታፊዎች እንዳሉት÷ ዕለቱ የአለም ፅልመት እንዲገፈፍ ያስቻሉ ነቢይ የተወለዱበት በመሆኑ በዓሉን በታላቅ ደስታና ድምቀት ማክበራቸውን ገልጸዋል ሲል የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.