Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ የህብረት ስራ ማህበራት በ6 ሚሊየን ብር መነሻ ካፒታል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ፌዴሬሽን መሠረቱ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበበ የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት የፋይናንስ እንቅስቃሴን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችላቸውን በ6 ሚሊየን ብር መነሻ ካፒታል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ፌዴሬሽን መሠረቱ።

ፌዴሬሽኑን የአዲስ አበባ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን እና የራስ አገዝ ሴቶች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየኖች በጋራ መስርተውታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 1 ሺህ 186 መሰረታዊ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ከሁለት ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ዩኒየኖች ጋር በመሆን በአዲስ አበባ የመጀመሪ የሆነውን የአዲስ አበባ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ፌዴሬሽን መስርተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብነህ እምሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እና አንድ ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብ ለመፍጠር በማስፈለጉ ፌዴሬሽኑ መመስረቱን ተናግረዋል።

በ6 ሚሊየን ብር መነሻ ካፒታል የተመሰረተው ፌዴሬሽን ለኅብረት ሥራ ማኅበራትና ዩኒየኖች የፋይናንስ ችግር እንዳያጋጥማቸው የቁጠባና ብድር፣ የኢንሹራንስ፣ የኦዲት፣ የአቅም ግንባታ እና ስልጠና አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን የኅብረት ሥራ ማኅበራትና ዩኒየኖች የሚገጥማቸውን የገንዘብ እጥረት እንደሚቀርፍም ገልጸዋል።

ፌዴሬሽኑ 10 አባላት እንዳሉት ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.