Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያው የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የንግድ አውሮፕላን እስራኤል አረፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመጀመሪያው የንግድ አውሮፕላን ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በመነሳት ለመጀመሪያ ጊዜ እስራኤል ማረፉ ተገለጸ፡፡

ሁለቱ ሃገራት ከአንድ ወር በፊት በአሜሪካ አሸማጋይነት ግንኙነታቸውን ዳግም ለማደስ መስማማታቸው ይታወሳል፡፡፡

ከስምምነቱ በኋላም በሃገራቱ ታሪክ የመጀመሪያው የንግድ አውሮፕላን ወደ እስራኤል በረራውን አድርጓል፡፡

በአንጻሩ የእስራኤል ቱሪዝም ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ወደ ተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ያቀናሉ ተብሏል፡፡

የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ንብረት የሆነው ኢትሃድ አየር መንገድ ጉዞውን ታሪካዊ ብሎታል፡፡

በቀጣይነትም በቋሚነት ወደ እስራኤል ለመብረር ማቀዱን በትዊተር ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.