Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔ ተካሄደ፡፡

ጉባዔው በኢትዮጵያ ሲካሄድ በዓይነቱ የመጀመሪያው ሲሆን፤ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ካዘጋጀው የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ጋር ተጣጥሞ የሚካሄድ ነው ተብሏል፡፡

በጉባዔው ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የትራንስፖርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

የትራንስፖርት እድገትን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ዘርፍ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው አንስተዋል፡፡

ይህንን ለማሳካት ከመንግስት በተጨማሪ የግል ባለሀብቶችን ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ምንም ያህል በግብርናም ሆነ  በማንኛውም የኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ እንደ ሀገር ስኬታማ ብንሆንም የትራንስፖርትና የሎጀስቲክስ ስኬት ካልታከለበት ውጤታማ አይሆንም ብለዋል፡፡

የግብርና ምርትንም ሆነ ማዳበሪያን ለማጓጓዝ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ አገልግሎቱ የዘመነና ፈጣን መሆን ትልቅ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ስራዎቻችን በቴክኖሎጂ መደገፍ አለባቸው ብለዋል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ በበኩላቸው መንግስት በኢኮኖሚዉ የግሉን ባለሀብት ለማሳተፍ ቁርጠኛነት ገልጸዋል፡፡

ብሔራዊ የትራንስፖርት ፖሊሲ የግሉን ዘርፍ በስፋት ማሳተፍ የሚቻልበትን ዘርፎች ለመለየት በሚያስችል መልኩ የተቃኘ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

በተጨማሪም ከ3 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚያስፈልገዉ የ10 ዓመት የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ የልማት ዕቅድን ማሳካት የሚቻልበት ዕዉቀትና የፋናንስ አቅም በመፍጠር በትራንስፖርት መሰረት ልማት፣ በትራንስፖርት አገልግሎትና አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት ለሀገራዊ የለዉጥ ጉዞ ስኬት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል።

በመድረኩ 44 ያህል ፕሮጀክቶች በመንገድ ልማት፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሎጂስቲክስ፣ በባቡርና በአየር ትራንስፖርት መስኮች መንግስት ከግሉ ዘርፍ ጋር ሊጣመር በሚችልባቸው እድሎች ላይ ምክክር ይደረጋልም ነው የተባለው።

የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ነው የሚካሄደው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.