Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያው የዛምቢያ ፕሬዚደንት የነበሩት ኬኔት ካውንዳ ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የመጀመሪያው የዛምቢያ ፕሬዚደንት የነበሩት ኬኔት ካውንዳ በ97 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል።

ኬኔት ካውንዳ በአገሪቱ የነጻነት ትግል ሲደረግ ቁልፍ ሰው እንደነበሩ ይነገራል።

ካውንዳ ሰኞ ዕለት በሳንባ ምች ህመም ምክንያት ሆስፒታል ገብተው የነበረ ሲሆን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።

ኬኔት ካውንዳ እአአ በ1950ዎቹ ዛምቢያን ከብሪታኒያ አገዛዝ ስር ነጻ ለማውጣት በሚደረገው ትግል ውስጥ ቁልፍ ሰው እንደነበሩ ይነገራል።

በ1964 የዛምቢያ ነጻ ስትወጣ ካውንዳ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት በመሆን ለ27 ዓመታት መርተዋታል።

ከ30 ዓመት በፊት በተካሄደውና በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሳተፉበት ምርጫ ከተሸነፉ በኋላ ሥልጣናቸውን አስረክበዋል።

ካውንዳ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የነበረው የዘር መድልኦ ሥርዓት እንዲያበቃ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸው ይነገራል።

ምንጭ:- ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.