Fana: At a Speed of Life!

የመጋቢት 27 የዐቢይ ፆም 7ኛ ሳምንት የሰንበተ ክርስቲያን ቅዳሴ ከጠዋቱ 11:30 ጀምሮ በአዲስ ቴቪ በቀጥታ ይተላለፋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመጋቢት 27 የዐቢይጾም 7ኛ ሳምንት የሰንበተ ክርስቲያን ቅዳሴ ከጠዋቱ 11:30 ጀምሮ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አዲስ ቴሌቪዥን በቀጥታ እንደሚተላለፍ ተገለፀ።

ዕለቱ ዓመታዊ የመድኅኔዓለም በዓል በመሆኑ ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን እንኳን አደረሳችሁ ያለዐው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ የተስፋ ልዑክ ዐቢይ ግብረ ኃይል በዕለቱ የማይቆርቡ ምእመናን ቅዳሴውን በቤታቸው በሱባኤ ባሉበት ሁነው እንዲሰሙ፣ በጸሎት እንዲተጉ በማሰብ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን ለማስተፈጸም የተደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ምእመናንም ወቅታዊውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል እየተወሰደ ካለው እርምጃ አንጻር በቤታቸው ሆነው ከቦሌ ደብረ ሳሌም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፈውን የንግስ በዓል እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቧል።

የዐቢይጾም 7ኛ ሳምንት የሰንበተ ክርስቲያን ቅዳሴ እና ዓመታዊ የቅዱስ መድኅኔዓለም በዓል በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት የሚተላለፈውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ምዕመናን በየቤታቸው በፀሎት እንዲወሰኑ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ምዕመናን በቤት ሆነው ኃይማኖታዊ ስነ ስርዓቱን እንዲከታተሉ በማሰብ መሆኑም ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.