Fana: At a Speed of Life!

የመጥፋት አደጋ የተደቀነባቸውን በዓላት ትውፊታቸውን ጠብቆ ማክበር እንደሚገበ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጥፋት አደጋ የተደቀነባቸውን በዓላት ትውፊታቸውን ጠብቆ ማክበር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው÷በዓላት እየተበረዙ ትውፊታቸው እየጠፋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በደብረ ታቦር ከተማ የሚከበረውን የቡሄ በዓል አስመልክተው አንደተናገሩት÷የመጥፋት አደጋ የተደቀነባቸውን በዓላት ትውፊታቸውን ጠብቆ ማክበር ያስፈልጋል ።

የኢትዮጵያ ሀይማኖታዊም ሆኑ ባህላዊ በዓላት በውጭ ባህል የመበረዘ እና የመጥፋት አደጋ ተደቅኖባቸዋል፣ከነዚህም ውስጥ ቡሄ አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ዩኒቨርስቲውም በዓላቶች ትውፊታቸው ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፉ የራሱን ሚና እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም የቡሄ በዓል ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ በደብረ ታቦር ከተማ እንዲከበር ዩኒቨርሲቲው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትልቅ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዋል።

ያለፈው ዓመት በጦርነቱና በኮቪድ 19 ምክንያት እንዳልተከበረ በማስታወስ ዘንድሮ በደማቅ ሁኔታ የሚከበር ይሆናል ነው ያሉት፡፡

ከተማው የበዓሉን ስም እንደመያዙ ደብረ ታቦርን በደብረ ታቦር ከተማ በሚል እንደሚከበር ታውቋል።

በታሪኩ ለገሰ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.