Fana: At a Speed of Life!

የሚስተዋለው መዘናጋት የኮቪድ19 ወረርሽኝ ስርጭት እንዲጨምር አድርጓል – ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር በህብረተሰቡ ዘንድ በሚስተዋለው መዘናጋት ሳቢያ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን አስታወቀ።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በኮቪድ19 ስርጭትና ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ አንድ አመት ሊሞላው ሳምንት እንደቀረው በማንሳት ቁጥሩ አሁን ላይ እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም 10 በመቶ የነበረው ስርጭትም 13 በመቶ መድረሱን ጠቅሰው፥ ባለፉት 10 ቀናትም ከ8 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ነው ያሉት፡፡
ባለፉት 10 ቀናት ብቻም 120 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል ነው ያሉት።
ለዚህም ሰዎች የሚሰበሰቡበት እንደ ሰርግ፣ ሃዘን ፣ ህዝባዊ በዓላት እና መሰል ህዝብ የሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች ቁጥሩ ከፍ እንዲል አስተዋፅዖ አድርገዋል ተብሏል፡፡
የፅኑ ህሙማን ቁጥር መጨመሩ የተገለጸ ሲሆን በክልሎችም የህክምና መስጫ ማዕከላትን የማስፋፋት ስራ ቢሰራም የአቅም ማነስ ችግር እንዳለም ተናግረዋል ሚኒስትሯ፡፡
በዚህም ህመምተኞችን በህክምና መዕከላት መርዳት እና መንከባከብ ከባድ ፈተና ሆኗል ብለዋል፡፡
“ሁሉም የመተንፈሻ መሳሪያዎች በህመመምተኞች ተይዘው ሌላው የጠናበት ህመምተኛ መሳሪያውን በሞት እና በሕይወት መካከል ሆኖ እየጠበቀ ነው” ብለዋል፡፡
የማስክ ተጠቃሚዎች ቁጥር መቀነሱን የተናገሩት ዶክተር ሊያ በአዲስ አበባ 54 በመቶ በሃገር ደረጃ ደግሞ 35 በመቶ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያም ሃይማኖታዊ በዓላት ላይ ፣ ስፖርታዊ ክንውኖች ላይ፣ የተለያዩ ዝግጅቶች፣ ካፌ እና ሬስቶራንቶች ላይ በአጠቃላይ ህዝብ የሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.