Fana: At a Speed of Life!

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አመራርና ሰራተኞች ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አመራርና ሰራተኞች በሆለታ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡
 
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ÷ምድርን አረንጓዴ የማድረግ ሥራ የሚድሮክ ቋሚና የዘወትር ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
የተቋሙ ሰራተኞች የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ እና በየጊዜው መጎብኘት እንዳለባቸው ስራ አስፈፃሚው አሳስበዋል፡፡
 
ችግኝ መትከል ከማህበራዊ ሃላፊነት በተጨማሪ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ነው ዋና ስራ አስፈፃሚው የገለጹት፡፡
 
አቶ ጀማል ሚድሮክ በሁሉም አካባቢዎች ባሉት እርሻዎች በየዓመቱ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን እንደሚተክል መግለጸቸውንም ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.