Fana: At a Speed of Life!

የማክሮ ኢኮኖሚውን በሚያሳድጉ ዘርፎች ላይ መስራት ይገባል- ባለሙያዎች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚ ሊያሳድጉ በሚችሉ ዘርፎች ላይ በስፋት መስራት ይገባል ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ተናገሩ።

የወጪ ንግድ መጠንን ከፍ ማድረግ፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን ማሳደግ እንዲሁም ምርትና ምርታማነት ማስፋፋት በትኩረት ሊሰራባቸው የሚገቡ ዘርፎች ናቸው ብለዋል ባለሙያዎቹ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የምጣኔ ሀብትባለሙያው ዶክተር ደግዬ ጎሹ እና አቶ ሙሀመድ ኢሳ፥ ግብርናውን ማዘመን እና በቴክኖሎጅ የተደገፈ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ ኢንቨስትመንትን የሚያበረታቱ ፖሊሲዎች ላይ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የተጀመሩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ማጠናቀቅም ለማክሮ ኢኮኖሚው እድገት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚውን ዘርፍ የሚፈትኑ የዋጋ ግሽበት፣ የሸቀጦች ዋጋ መዋዥቅ፣ በአቅርቦትና ፍላጎት መካከል ሰፊ ልዩነት መኖር፣ የስራ አጥነት ጫና እና የመሳሰሉ ክፍተቶችን በመለየትም መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በዙፋን ካሳሁን

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.