Fana: At a Speed of Life!

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ናቸው።

ስምምነቱ ከኢትዮጵያ ማዕድን ሀብትና ከዘርፉ ጋር የተጣጣሙ እንዲሁም በማዕድን ዘርፍ በከፍተኛነት የተለዩ የእውቀት ዘርፎችን በመለየት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኩል ስርዓተ ትምህርት እንዲዘጋጅላቸው እና ለባለሙያዎች እንዲሰጡ የሚያስችል ነው ተብሏል።

በማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ ዙሪያ በቀጣይነትም ፍላጎትን መሰረት ባደረገ መልኩ ተጨማሪ አዳዲስ የትምህርት ዘርፎችን በማዘጋጀት መደበኛ ትምህርት እና አጫጭር ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ነው የተገለጸው።

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብት የታደለች ብትሆንም በሃብት ላይ መቀመጥ ለብቻው ሃብታም አያደርግም ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ ከምድር በታች ያሉ ሃብቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ እና የባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት ያለውን ሃብት በአግባቡ መጠቀም መጀመር ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ባለሙያዎች የትምህርት ዕድል ማግኘት በሚችሉበት መንገድ ዙሪያ የተደረገው ስምምነትም የዚሁ አንድ አካል መሆኑን ኢንጂነር ታከለ በመድረኩ መናገራቸውን ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.