Fana: At a Speed of Life!

የምሥራቅ አፍሪካ የናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 34ኛው የምሥራቅ አፍሪካ ናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በስብሰባው የውሃና እና ኤነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ተሳትፈዋል፡፡

ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የናይል ተፋሰስ የምሥራቅ አፍሪካ አባል ሀገራት ቀጠናዊ የቴክኒክ ጽ/ቤት ምንም እንኳ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም፥ ለአባል ሀገራት የኢንቨስትመንት ፕሮግራሞችን ተደራሽ ከማድረግ እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ከመስራት ጀምሮ በሳይንስና በፖሊሲ ምክክሮች ላይ አበረታች ስራ ለመስራት መቻሉን ጠቁመዋል።

የተፋሰሱ አባል ሀገራት ለናይል ልማት የሚያደርጉት ትብብርና ቁርጠኝነት ቅድሚያ ትኩረት እንደሚያስፈልገውም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ ናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት ኢትዮጵያ፥ ግብፅ፣ ሱዳንነና ደቡብ ሱዳን መሆናቸው ይታወቃል።

የናይል ተፋሰስ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ቀጠናዊ የቴክኒክ ዋና ጽ/ቤት አዲስ አበባ እንደሚገኝም ከውና እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አስታውሷል፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.