Fana: At a Speed of Life!

የምርጫ አዘጋገብ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለጋዜጠኞች እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርጫ አዘጋገብ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለጋዜጠኞች እየተሰጠ ነው።

ዩ ኤስ ኤጀንሲ ፎር ግሎባል ሚድያ እና የአሜሪካ ድምፅ ናቸው ስልጠናውን ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች እየሰጡ ያሉት።

በስልጠናው ላይ ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ተአማኒነት እና ዴሞክራሲያዊነት የመገናኛ ብዙሃን ሚናን በተመለከተ ውይይት ተካሂዷል።

መራጩ ህብረተሰብ እውነተኛ መረጃን መሰረት ባደረገ አኳኋን እንዲመርጥ የሚያግዙ መረጃዎችን ለህዝቡ ማድረስ አስፈላጊነትና ተግባሩም ተቃኝቷል።

በምርጫ አዘጋገብ ወቅት ሊገጥሙ በሚችሉ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያም ጠቃሚ ልምዶች ተነስተዋል።

ይዘትን መሰረት ያደረገ አዘጋገብ፣ የፖለቲከኞች ክርክር እና ፍጭት ሃሳብ እና አማራጭ ይዞ መቅረብ ላይ እንዲያተኩር ያለው አጋዥነትም በስፋት ተነስቷል።

የመረጃን እውነተኝነት የማጣሪያ መንገዶች እና አስፈላጊነቱን አስመልክቶም ሰፊ ገለፃ ተደርጓል።

የምርጫ አዘጋገብ ሙያዊ ስነምግባርና ሃላፊነትን ያስቀደመ መሆን ለምርጫው ሰላማዊነት እና ዴሞክራሲያዊነት ያለው ሚናም ታይቷል።

ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው የመገናኛ ብዙሃን እና ጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የስነ ምግባር እና አሰራር መመሪያ እና የኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና፣ የምርጫ ስነምግብር አዋጅ ላይ የተቀመጡ ነጥቦችንም በስፋት ተዳሰዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ያነጋገራቸው የስልጠናው ተሳታፊዎችም መሰል ስልጠናዎች ቀድመው የተሰጡ እንደመሆናቸው በስራው ወቅት ሊያጋጥሙ ለሚችሉ ሁኔታዎች ጋዜጠኛው ራሱን እንዲያዘጋጅ ይጠቅማል ብለዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.