Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የዱር እንስሳት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ለመቆጣጠር የሚሰራውን ኃይል እንዲቀላቀሉ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ዐቃብያነ-ሕግ ማሕበር ስድስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አባላት በምስራቅ አፍሪካ የዱር እንስሳት ላይ የሚፈፀመውን ወንጀል ለመከላከል የሚሰራውን ኃይል እንዲቀላቀሉ ጠየቀ፡፡

ማሕበሩ የዱር እንስሳት ላይ የሚፈፀመው ወንጀል የቀጠናው የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ነው የገለፀው፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ዐቃብያነ-ሕግ ማሕበር በአባል ሀገራቱ መካከል ትብብር እንዲጠናከር በቀጠናው የሚስተዋሉ ወንጀሎችን የመለየት፣ የመመርመርና ክስ የመመስረት ኃላፊነት ወስዶ ይሰራል፡፡

በ9ኛው የምስራቅ አፍሪካ ዐቃብያነ ሕግ ማሕበር ዓመታዊ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ በዱር እንስሳት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቁ በመምጣታቸው የማሕበሩ አባል ሀገራት በጋራ መስራት ይገባቸዋል ብሏል፡፡

የማሕበሩ አባል ሀገራት ታንዛኒያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ርዋንዳ፣ ብሩንዲ እና ደቡብ ሱዳን ሲሆኑ÷ ሀገራቱ መረጃዎችን በመለዋወጥ ረገድ እንዲተባበሩ እና ወንጀለኞችን በማጋለጥ ለፍርድ እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.