Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል የምርጫ ታዛቢ ቡድኑን ወደ ኢትዮጵያ ላከ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል የምርጫ ታዛቢ ቡድኑን ወደ ኢትዮጵያ መላኩን አስታወቀ፡፡

ታዛቢ ቡድኑ ከኢትዮጵያ በቀረበለት ግብዣ መሰረት ምርጫውን ለመታዘብ ወደ ኢትዮጵያ መላኩን የተጠባባቂ ሃይሉ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ጌታቸው ሽፈራው ገልጸዋል፡፡

ታዛቢ ቡድኑ ከአባል ሃገራቱ የተውጣጣና 28 አባላት ያሉት ሲሆን፥ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋር፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ክልል፣ ድሬ ዳዋ እና በአዲስ አበባ ተዘዋውሮ የምርጫውን ሁኔታ የሚከታተል ይሆናል፡፡

ታዛቢ ቡድኑ በአፍሪካ ህብረት የዴሞክራሲ፣ የምርጫ እና አስተዳደር መርህ መሰረት ምርጫውን እንደሚታዘብ ተጠባባቂ ሃይሉ ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ አንጻርም ታዛቢ ቡድኑ ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ዓለም አቀፍ የምርጫ መርሆዎችን ባከበረ መልኩ መካሄድ አለመካሄዱን እንዲሁም የምርጫውን ግልጽነትና ታማኝነት በመከታተል በምርጫው ሂደት ዙሪያ ሪፖርት የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.