Fana: At a Speed of Life!

የምንፈልገው ኢትዮጵያዊ መሆን ወይም ኢትዮጵያ መሆን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምንፈልገው ኢትዮጵያዊ መሆን ወይም ኢትዮጵያ መሆን ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከግንባር ሆነው በሰጡት መግለጫ÷የወገን ጦር በከፍተኛ ሞራልና ወኔ እየተዋጋ በጠላት እጅ ስር የነበሩ ቦታዎችን እየተቆጣጠረ መሆኑን አስታውቀዋል።
 
በዚህም አሁን ላይ የመከላከያ ሰራዊት ካሳጊታን መቆጣጠሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ቡርቃ እና ጭፍራን ዛሬ እንደሚቆጣጠርም ጠቁመዋል።
 
በጦር ግንባር ተገኝተው የቅርብ አመራር እየሰጡ ያሉት የኢፈዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዚሁ መግለጫው፥ ጦርነቱ በከፍተኛ ድል እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፥ እስከትናንትና ድረስ በጠላት እጅ የነበረው የካሳ ጊታ ተራራ ሙሉ በመሉ በወገን ጦር ቁጥጥር ስር ውሏል።
 
በዛሬው ዕለት ጭፍራንና ቡርቃን እንይዛለን፥ ድሉ ይቀጥላል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
 
የሰራዊቱ የውጊያ ሞራል እጅግ ደስ እንደሚል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ወራሪውን ጠላት እስክንቀብርና የኢትዮጵያ ነፃነት እስኪረጋገጥ ድርስ ወደ ኋላ አንልም ነው ያሉት።
 
ይህንንም በአገር ውስጥና በውጭ ያለው ህዝባችን ከጎናችን በመሆኑ በድል እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን ብለዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ መግለጫቸው፥ “የምንፈለገው፥ እኛ ሞተን የምትኩረራ እትዮጵያን ማየት ነው፤ የምንፈልገው ኢትዮጵያዊ መሆን ወይም ኢትዮጵያ መሆን ነው” ሲሉም አስምረውዋል ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመጀመሪያው በዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉትና ከፍተኛ አድናቆት በተቸረው ንግግራቸው “ እኛ ኢትዮጵያውያን በህይወት ስንኖር ኢትዮጵያዊ፥ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ እንሆናለን “ ማለታቸው ይታወሳል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.