Fana: At a Speed of Life!

የምክር ቤቱ አባላት የህወሓት የጥፋት ቡድን እና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባውን አካሄደ።

ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት አካሄዷል።

የምክር ቤቱ አባላት የህወሓት የጥፋት ቡድን እና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ጠይቀዋል።

ሁለቱ ቡድኖች በቅንጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሽብር ድርጊት ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን ገልፀው በጥፋታቸው እንዳይቀጥሉም በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ነው አባላቱ የጠየቁት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.