Fana: At a Speed of Life!

“የምክንያታዊ ወጣት መድረክ” በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የምክንያታዊ ወጣት መድረክ” በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በአዲስ አበባ ተካሄደ።

በኦሮሞ ባህል ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው በዚሁ መድረክ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካበቢዎች የተውጣጡ ከ300 በላይ ወጣቶች ተሳትፈውበታል።

መድረኩ “የሀገረ መንግስት ፣ ብሄረ መንግስት ግንባታና ዓለም አቀፋዊ ልምዶች” የሚል ርዕስ ላይ ትኩረት አድርጎ መክሯል።

በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ መነሻ ፅሁፍ የቀረበ ሲሆን፥ ወጣቱ ሲቃወምም ሆነ ሲደግፍ በምክንያት ሊሆን እንደሚገባ የሚያመላክቱ ዓለም አቀፋዊ ልምዶች ቀርበው ተዳሰዋል፡፡

የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ፓለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አድናን ሃጅ በመድረኩ የዴሞራሲ ምህዳሩ መስፋቱ ያለወጣቱ ምክንያታዊነትና ንቁ ተሳትፎ ዋጋ እንደሌለው ተናግሯል፡፡

ወጣቶች በተጀመረው ለውጥ ውስጥ የማይተካ ሚናቸውን እንዲወጡ እውቀት እና ልምድን መሰረት ያደረገ ምክንያታዊነት እንደሚያስፈልግም ገልጿል፡፡

መድረኩም በዋናነት እውቀት እና ልምድን መሰረት ያደረገ ምክንያታዊነትን መፍጠር ያለመ መሆኑንም አስታውቋል።

ለወጣቱ መሰል መድረኮች መዘጋጀታቸው አስፈላጊነታቸው የጎላ መሆኑም በመድረኩ ላይ ተነስቷል፡፡

በውይይቱ ከወጣት አደረጃጀትና ከንግዱ ማህበረሰብ የመጡ እንዲሁም ምሁራን እና የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡

በሀብታሙ ተክለስላሴ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.