Fana: At a Speed of Life!

የምዕራብ ዕዝ የሽብር ቡድኑን ህወሓት ለመደምሰስ በሁሉም ዘርፍ አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል-ብ/ጀነራል ሰይድ ትኩዬ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ዕዝ የሽብር ቡድኑን ህወሓት ለመደምሰስ በሁሉም ዘርፍ አስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ብርጋዴር ጄነራል ሰይድ ትኩዬ ገለፁ፡፡

የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ሰይድ ትኩዬ÷ ማይጠብሪ ግንባር ያለውን የሎጅስቲክስ አቅርቦት አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የምዕራብ ዕዝ በማይጠብሪ ግንባር ያለውን የሽቡር ቡድን ለመደምሰስ አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።

በዚህ መሰረትም ከከባድ መሳሪዎች ጀምሮ የተኳሽ ጥይቶች አቅርቦት በተሟላ ደረጃ ዝግጁ መሆኑን አንስተዋል።

የሰው ሃይልን አስመልክቶም የሀገር መከላከያ ሰራዊት የክልል ልዩ ሃይሎች፣ ሚሊሻና ፋኖዎች ጋር አስተማማኝ ቅንጅት መፍጠሩን ተናግረዋል።

የጦር መሳሪያ ስርጭቱ በተሳለጠ ሁኔታ እየተከናወነ እና ጥቅም ላይ አየዋለ ነው ነው ያሉት ብርጋዴር ጀነራል ሰይድ፥ይህም እስካሁን ለተገኘው ድል ጉልህ ሚና መጫዎቱን አውስተዋል።

የደባርቅ እና የአካባቢው ማህበረሰብ ለሰራዊት ያለውን ደጀንነት በሚገባ እያስመሰከረ መሆኑንም ተናግረዋል።

ይህም ለመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልል ልዩ ሃይሎች ከፍተኛ የሞራል ስንቅ መሆኑን ነው የገለጹት።

አሁን ላይ የሽብር ቡድኑ በሰራዊቱ በደረሰበት ከባድ ምት ወሯቸው የነበሩ አካባቢዎችን ጥሎ እፈረጠጠ ነው ያሉት ምክትል አዛዡ፥በቅርቡም አከርካሪውን በመስበር የመደምሰስ ስራ ይከናወናል ብለዋል።

ለዚህም የምዕራብ ዕዝ ዝግጁነቱን አጠናቆ ትዕዛዝ እየተጠባበቀ መሆንን ገልጸዋል።

በመላኩ ገድፍ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.