Fana: At a Speed of Life!

የምግብ ዘይትን በአግሮ አንደስትሪ ኩታ ገጠም እርሻዎች አማካኝነት የማምረት ሥራ መጀመር ለአምራቾቹ ትርፋማነትን ያስገኛል- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የምግብ ዘይትን በአግሮ አንደስትሪ ኩታ ገጠም እርሻዎች አማካኝነት የማምረት ሥራ መጀመር ለአምራቾቹ ትርፋማነትን ያስገኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ዶክተር ዐቢይ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያ ወደ ውጪ በመላክ የውጪ ምንዛሬ ከምታገኝባቸው ዋነኛ ምርቶች መካከል የዘይት እህሎች ይገኙበታል  ብለዋል፡፡

የዘይት እህሎችን በማምረት እና በማሠራጨት ሂደትም ከ3 ሚሊየን የሚበልጡ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች  እንደሚሳተፉበት ጠቁመው÷እንዲያም ሆኖ ኢትዮጵያ የምግብ ዘይትን በከፍተኛ መጠን ከውጪ ከሚያስገቡ ሀገራት መካከል አንዷ ናት ብለዋል።

በዚህም ከ95 በመቶ የሚበልጠው የሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚሸፈነው ከውጪ ሀገራት በሚገባ ዘይት አማካኝነት መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም በየዓመቱ ዘይትን ከውጪ ሀገራት ለማስገባት የሚወጣው አማካይ የገንዘብ መጠን ከ400 ሚሊየን ዶላር ይበልጣል  ነው ያሉት፡፡

ጎጃም በሚገኙት የቡሬ ዳሞት እና የደብረ ማርቆስ አካባቢዎች የግሉ ዘርፍ የምግብ ዘይትን በአግሮ አንደስትሪ ኩታ ገጠም እርሻዎች አማካኝነት የማምረቱን ሥራ በመጀመር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ሥራው ቀጣይ የምርት ሂደቶች እንዲሳኩ ለማድረግ የሚያስችል ሲሆን÷ ምርቱ ደግሞ ለኩታ ገጠም አምራቾቹ ትርፋማነትን  የሚያስገኝ ነው ብለዋል፡፡

ከዚያም ባለፈ በዶሮ እርባታ፣ በወተት እና የወተት ተዋጽዖ ምርቶች እንዲሁም ከብት በማደለብ ተጨማሪ ሥራዎችን ለመፍጠርም ያስችላል ነው ያሉት፡፡

በዚህ መልኩየሀገር ውስጥ ፍጆታን መሸፈን እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ይቻላል ብለዋል፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.