Fana: At a Speed of Life!

የምግብ ደህንነትን እና የግብርና ምርታማነትን ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ የገጠር ልማትን እያስፋፋች ነው- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ኢትዮጵያ የምግብ ደህንነትን እና የግብርና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የገጠር ልማትን እያስፋፋች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገለፁ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው የአዳጊ ሀገራት ቡድን ዓመታዊ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል።

ስብሰባው የአዳጊ ሀገራትን ቀዳሚ ቀጣይነት ያለው እድገት ለመለየት እና ለኢስታንቡል የድርጊት መርሃ ግብር የመጨረሻ አመት አፈፃፀም ስትራቴጂክ መመሪያዎችን ለማቅረብ ያለመ ነበር።

በዚህ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን እና የኢስታንቡል የድርጊት መርሃ ግብርን ማሳካት እንዳትችል ችግር የፈጠሩ ጉዳዮችን አቅርበዋል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝም በአዳጊ ሀገራት የተመዘገቡ የልማት ውጤቶች ማዳከሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ገልፀዋል።

ድህነት ፣ ስራ አጥነት እና ዘርፈ ብዙ የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች መዋቅራዊ በሆነ መንገድ በአዳጊ ሀገራት ተግዳሮት መፍጠር እንደቀጠሉም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ እነዚህ ችግሮች ቢኖሩም የምግብ ደህንነትን እና የግብርና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የገጠር ልማትን እያስፋፋች እንደሆነ ተናገረዋል።

የ2030 የልማት ግቦችን ለማሳካትም ኢትዮጵያ ማህበራዊ እና አካላዊ መሰረተ ልማቶች ላይ መዕዋለ ነዋይ ፈሰስ እያደረገች እንደሆነም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

በዘላቂ የልማት ግቦች ከተቀመጠው ግብ አንፃር የአዳጊ ሀገራት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የ2030 አጀንዳ እና የኢስታንቡል የድርጊት መርሃ ግብርን ውጤታማ በመሆነ መንገድ ለመተግበር እንደገና መስራት ይገባል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.