Fana: At a Speed of Life!

የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ፍቃድ ለውጪ ኩባንያዎች ያልተሰጠበት ምክንያት ከብሔራዊ ደህንነት እና ጥቅም አንጻር ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ፍቃድ ለውጪ ኩባንያዎች ያልተሰጠበት ምክንያት ከብሔራዊ ደህንነት እና ጥቅም አንጻር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ይህንን ያሉት ኢትዮ ቴሌኮም ”ቴሌብር ” የሞባይል የክፍያ ስርዓትን በይፋ በተጀመረበት ስነ ስርዓት ላይ ነው፡፡
ለውጪ ኩባንያዎች ፍቃዱ ባለመሰጠቱ ኢትዮጵያ 500 ሚሊየን ዶላር ታጣለች ብለዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን የማካካስ ስራ እንደሚሰራ እምነታቸውን እንደሆኑ በማንሳት የፋይናስ ፖሊሲ ማሻሻዎች መደረጋቸው ለቴሌኮም ዘርፍ ማድግ ትልቅ ፍይዳ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ከሌሎች ኦፕሬተሮች ጋር መወዳደር የሚያስችል አቅም እስኪፈጥር  የአንድ  ዓመት ጊዜ የተሰጠው ሲሆን÷ከአንድ ዓመት በኋላ ለሌሎች ኦፕሬተሮችም የአገልግሎቱ ፍቃድ ክፍት እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.