Fana: At a Speed of Life!

የሞደርና ክትባት አዲስ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ እንደሚከላከል ተመራማሪዎች አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞደርና ክትባት በብሪታንያና በደቡብ አፍሪካ የተከሰተውን አዲሱን የኮሮና ቫይረስ እንደሚከላከል የመድሃኒት አምራች ኩባንያ ተመራማሪዎች አረጋገጡ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ሙከራዎች እንዳሳዩት ከሆነ ክትባቱ አዲሱ ቫይረስን ለመከላከል የሚረዳ የሰውነት የመከላከል አቅምን ማዳበር መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡

ተመራማሪዎቹ በዚህ ጥናት የሞደርናን ክትባት የወሰዱ የስምንት ሰዎችን የደም ናሙና መውሰዳቸውን ነው የተናገሩት፡፡

በሌላ በኩል አዲሱ ቫይረስ ወደ ተለያዩ ዓለም ሃገራት በፍጥነት እየተዛመተ እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡

ይህ በፍጥነት የሚዛመተው ቫይረስ ከቀደመው ይልቅ የሰውነት ህዋስን እንደሚያዳክም ነው የተገለጸው፡፡

አሁን የሚገኙት ክትባቶች መጀመሪያ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ መሰረት አድርገው የበለጸጉ ናቸው ተብሏል፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.