Fana: At a Speed of Life!

የሞጆ- መቂ-ባቱ የክፍያ መንገድ ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞጆ- መቂ-ባቱ 92 ኪሎ ሜትር የክፍያ መንገድ በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
የሞጆ ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው የክፍያ መንገዱ÷ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ እና የትራንስፖርት ሚንስቴር ዲኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በተገኙበት ነው ለአገልግሎት ክፍት የሆነው፡፡
የፍጥነት የክፍያ መንገዱ በ6ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጭ የተገነባ መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ለ7 አመታት ሲያስተዳድረው ከቆየው የአዲስ አበባ አዳማ እና የድሬደዋ ደወሌ የክፍያ መንገድ በመቀጠል ወደ ስራ የገባ 3ኛው የክፍያ መንገድ ነውም ተብሏል፡፡
መንገዱ በሚያዚያ ወር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መመቀረቁ የሚታወስ ሲሆን÷ የክፍያ ቴክኖሎጂዎችን ለማሟለት ሲባል አገልግሎቱ መዘግየቱ በመርሃ ግብሩ ተገልጿል፡፡
በለይኩን አለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.