Fana: At a Speed of Life!

የሥራ ዕድል ፈጠራን በበቂ ሁኔታ ለማመቻቸት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ያለው ብቃት ሊጠናከርና ሊፋጠን ይገባል-ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ዕድል ፈጠራን በበቂ ሁኔታ ለማመቻቸት፣ መሥሪያ ቤቱ ያለው ብቃት ሊጠናከርና ሊፋጠን ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በቅርቡ የተቋቋመ ተቋም እንደ መሆኑ፣በ10 ወራት ውስጥ ብቻ በሚያስደንቅ ሁኔታ ራሱን አዋቅሮ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሥራና ክሂሎትን የመፍጠር ተልዕኮውን በብቃት መከወን ጀምሯል ብለዋል።
የሥራ ዕድልን ማመቻቸት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ይህንኑ የሚያሳልጥ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የተቋቋመው የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግዳሮቶችን በብቃት ለመወጣት እንዲሁም የሠለጠነ የሰው ኃይልና የአገልጋይነት አመለካከት ያላቸውን አገልጋዮችን ለማብቃት እንዲቻል መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ዕድል ፈጠራን በበቂ ሁኔታ ለማመቻቸት፣ መሥሪያ ቤቱ ያለው ብቃት ሊጠናከርና ሊፋጠን ይገባል ነው ያሉት፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.