Fana: At a Speed of Life!

የረመዳን ጾምን እና የፋሲካ በዓልን መሰረት በማድረግ ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ ሸቀጦች የሟሟላት ስራ ተጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)- የረመዳን ጾምን እና የፋሲካ በዓልን መሰረት በማድረግ ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ ሸቀጦች የሟሟላት ስራ ጀምሬአለው አለ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ፡፡

ቢሮው ይህን ያለው  ጣቢያችን በዛሬው እለት በመዲናዋ የሚገኙ ከ800 በላይ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆችን መካከል በርካታ ተጠቃሚዎች የሚገበያዩበት በቂርቆስ: በልደታ: የካን  ጨምሮ   በቦሌ ወረዳ 9 በሚገኙ የሸማች ማህበራት ሱቆችን ተዘዋውሮ ቅኝት ማድረጉን ተከትሎ ነው።

ይሁንና በተዘዋወርንባቸው የሸማች ማህበራት ሱቆች የፈሳሽ የምግብ የዘይት እጥረት መኖሩን የተመለከተ ሲሆን፣ አልፎ አልፎ  በቆጠራ ምክንያት የስኳር ሽያጭ አለመከናወኑን እና  ሌሎች ግብአቶች ግን መኖራቸውን ተመልክተናል።

የከተማ አስተዳደሩ 50 ሺህ ኩንታል ጤፍ  የነጭ መለስተኛ በኪሎ ከ38 ብር ጀምሮ በማህበራቱ በኩልጨለሽያጭ ቀርቧል።

ስንዴ ከ10 ሺህ ኩንታል  በላይ የቀረበ ሲሆን ሌሎች ለረመዳን ጾም እና ለፋሲካ በዓል አስፈላጊ ግብአቶች የማሟላት ስራ መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አከበረኝ ወጋገን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ያነጋገርናቸው ሸማቾች በአንዳንድ ማህበራት አልቋል እየተባለ በትውውቅ እና አየር በአየር  ዘይት እንደሚሸጥ መናገራቸውን ተከትሎ በአሁን ወቅት እንደዚህ አይነት ተግባር የሚፈጽሙትን በመከታተል እርምጃ መውሰድ የሚያስችል  በምክትል  ከንቲባ ወ/ ሮ አዳነች ሀቤቤ  አስተባባሪነት  የሸማች ጥበቃ  ግብረ ሀይል ተቋቁሞ  ወደ ስራ ለመግባት በዝግጅት ላይ መኋናቸውን አክለዋል።

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.