Fana: At a Speed of Life!

የሮቦት ዶክተር ወደፊት ወረርሽኝ ሲከሰት የህክምና እርዳታ መስጠት እንደሚችል ባለሙያወች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኤነድብራህ የሚገኙ የሮቦቲክስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተመራማሪዎች የዓለማችን የመጀመሪያ የሆነ በአንድ ጊዜ ከአንድ ሰው በላይ የህክምና እርዳታ የሚሰጥ ሮቦት ለመፍጠር እየሰሩ ይገኛሉ።

ሮቦቱ በእድሜ የገፉ ሰዎችን ለማገዝ በማሰብ መስራት ቢጀመርም ወደፊት ግን እንደ ኮሮና ያሉ ወረርሽኞች በሚከሰቱበት ጊዜ ሊያገለግሉ ይችላሉ ነው የተባለው።

አዲሱ ፕሮጀክት በአውሮፓ ህብረት ሆሪዞን 2020 የሚደገፍ ሲሆን፥ ሮቦቶች ከሰው ልጅ በተሻለ ፍጥነትና ክዋኔ በአንድ ጊዜ ከበርካታ ሰወች ጋር ውይይት በማድረግ ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉትን ወረርሽኞች ለመቆጣጠር ሊረዱ እንደሚችሉ ነው የኤድንበርግ የዘርፉ ባለሙያዎች የገለጹት።

ፕሮጀክቱ በመጀመሪያ ይዞት የተነሳው ዋና ዓላማ ይህ አልነበረም ያሉት የሄርዮት ዋት የኮምፒዩተር ሳይንስ ፕሮፌሰር ኦሊቨር ሌመን ሆኖም አሁን አለምን እያስጨነቀ ካለው ወረርሽኝ ጋር ተያያዠነት እንዳለው ተናግረዋል።

ሮቦቶቹ ቀደም ብለው በአንዳንድ ሆስፒታሎች ውስጥ እየሠሩ ቢሆንም፤ በአብዛኛው የተለያዩ እቃወችን ማቅረብ እና ታካሚወችን የሚመዘግቡ ብቻ መሆናቸው ነው የተገለጸው።

ፕሮጀክቱ ማህበራዊ መስተጋብር ሊፈጥሩ የሚችሉ አዳዲስ ሮቦቶችን በመፍጠር ለህክምናው ዘርፍ እንዲረዱ ይደረጋል ተብሏል።

ሮቦቶች ከእጅ እና ከተለያዩ ንክኪወች ነጻ ስለሚሆኑም  ተፈላጊ መሆናቸው በተደጋጋሚ ይነሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.