Fana: At a Speed of Life!

የሰላምና የደህንነት ሥራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ ተጠቆመ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ሊጠናከሩ ይገባል ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢዜማ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አንድነት ሽፈራው እና  የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር አቶ ገብሩ በርሄ ÷ ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበሩ ዶክተር አብዱል ቃድር አደም በበኩላቸው÷  በሀገር ውስጥ ያሉ የስጥ ችግሮች ለውጭ ኃይሎች መጠቀሚያ መሳሪያ እንዳይሆኑ ልዩ   ትኩረት ሊሰጠው  ይገባል ብለዋል፡፡

ለአገራችን ዘላቂ ጥቅምና እንድነት እንዲሁም ለአስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት የሰላም አማራጮችን የመጠቀም  ጉዳይ ሊበረታታ እንደሚገባም ነው ዶክተር አብዱል ቃድር የጠቆሙት፡፡

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ ሰላምና መረጋጋትን የማረጋገጡ ሥራ ለአንድ ወገን የሚተው ተግባር  አለመሆኑን ጠቁመው፥ ለጋራ ጥቅማችንና ለአገራችን ሰላም በጋራ ልንሰራ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በመንግስት በኩል የሰላምና የደህንነት ሥራዎችን በሚመለከት ሕዝቡን የበለጠ ማሳተፍ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ጠንካራ ሥራዎችን መሥራትና ዘላቂ መፍትሄ ላይ ማተኮር እንደሚገባም አመራሮቹ ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.