Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በሃገራዊ ሰላምና የህግ የበላይነት መከበር ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።

የምክክር መድረኩ “ነጋዴው ማህበረሰብ ለሃገራዊ የሰላም ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።

በመድረኩ ላይ ሴት ነጋዴዎች ለሃገራዊ ሰላም መጠበቅ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።

በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች በንግድ ሂደቱ ላይ ተዕፅኖ እየፈጠሩ መሆኑም በመድረኩ ተነስቷል።

ነጋዴዎችም ወጣቱን በኢኮኖሚ በመደገፍና በማሳተፍ ወደ ግጭት እንዳይገባ ማድረግ ይገባቸዋልም ነው የተባለው።

በመድረኩ ላይ የመወያያ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

መድረኩ የሰላም ሚኒስቴር፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የንግድ ዘርፍ ማህበራት እና የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበራት በትብብር ያዘጋጁት ነው።

በዘቢብ ተክላይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.