Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተመድና ከዓለም ዓቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ተወካዮች ጋር በበይነመረብ ውይይት አካሂዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ከሌሎች ዓለም ዓቀፍ የግብረ-ሰናይ ድርጅት ተወካዮች ጋር በበይነመረብ ውይይት አካሂዱ።

ሚኒስትሯ በውይይቱ የኢትዮጵያ መንግስት ከህግ ማስከበሩ ሂደት ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል የሚካሄደውን የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ስርጭት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የእርዳታ ስርጭቱ መጠን በየወቅቱ እያደገ መምጣቱን አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ህዝቡን ማገልገል እየጀመሩ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ ይሁን እንጂ አንዳንድ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ይህንን እውነታ ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በግልጽ ከማስረዳት አኳያ በቂ ስራ እየሰሩ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ከዚህ አኳያ ዓለም ዓቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች በመሬት ላይ ያሉትን እውነታዎች ሳያዛቡ፣ ሳይጨምሩና ሳይቀንሱ እንዲያሳውቁም ነው ያሳሰቡት።

በውይይቱ ከዓለም ዓቀፍ የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ተወካዮች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም ሚኒስትሯ ምላሽ መስጠታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.