Fana: At a Speed of Life!

የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያሪክ ኤሪኔጅ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሪ ፓትሪያሪክ ኤሪኔጅ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በ90 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

ፓትሪያሪኩ ባለፈው ወር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ባለፈው ሊቀ ጳጳስ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ከታደሙ በኋላ በተደረገላቸው ምርምራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው ነበር።

ይህንንም ተከትሎም ቤልግሬድ በሚገኝ ወታደራዊ ሆስፒታል የህክምና ክትልል ሲደረግላቸው ቆይቷል።

የፓትሪያሪኩን ህልፈት ይፋ ያደረጉት የሰርቢያ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ቩቺ “አንቱን በማወቄ እድለኛ ነኝ እንደ እርስዎ አይነት ሰው መቼም ከጎን አይለይም ብለዋል።

የፓትሪያሪኩ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ ባለፈው ማክሰኞ የመተንፈሻ መሳሪያ ተገጥሞላቸው እንደነበረ ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል።

ፓትሪያሪኩ ምንም አይነት ምልክት ሳያሳዩ እና በመልካም ጤንነት ላይ በነበሩበት ወቅት ካለባቸው የልብ በሽታ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ትኩሳት ማሳየታቸውን እና የጤናቸው ሁኔታም መዛባቱን የሰርቢያ ቤተክርስቲያን ማስታወቋን የኤ ኤፍ ፒ ዘገባ ያሳያል።

ፓትሪያሪኩ በወግ አጥባቂነታቸው የሚታወቁ ሲሆን በሰርቢያ ፖለቲካም ከፍ ያለ ተፅዕኖ እንዳላቸው ይነገራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.