Fana: At a Speed of Life!

የሰርግ ወጪያቸውን ለተፈናቃዮች ያደረጉት ኢትዮጵያዊትና ኤርትራዊ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ምዕራብ አውስትራሊያውያኑ ኢትዮጵያዊትና ኤርትራዊ ተጋቢ ሙሽሮች 10 ሺህ ዶላር የሰርግ ወጪያቸውን ለኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች ለገሱ፡፡

ኢትዮጵያዊቷ ሙሽሪት ብዙዓለም (ሊሊ) ተገኔ እና ኤርትራዊው ሙሽራ ዳንኤል ባህታ የሠርግ ወጪያቸውን ለኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች እንዲደርስላቸው በፐርዝ ምዕራብ አውስትራሊያ ልዩ የመስቀል በዓል ዝግጅት ላይ ቸረዋል።

ሙሽሪት ሊሊ “ኢትዮጵያ አገራችን በተለያዩ ችግሮችና ረሃብ ውስጥ ባለችበት ወቅት የምንደርስላት እኛ ነን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን በቃሽ እንዲላትና ጋብቻንንም እንዲባርክልን በፀሎታችሁ አስቡን” ብላለች፡፡

ሙሽራ ዳንኤል ባህታ “ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አንድ ነን፤ ችግሩ የጋራችን ነው” ማለቱንም ኤስ ቢ ኤስ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.