Fana: At a Speed of Life!

የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል ጥር 23 ይከበራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓልን ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ፡፡

የምስረታ በዓሉም ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ይከበራል፡፡

በአድዋ ጦርነት ወቅት ለሀገራቸው ነፃነት የተዋደቁ ፈረሰኞችንና ፈረሶችን ለመዘከር በ1933 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር ባህላዊ እሴቱን፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አበርክቶውን እንደጠበቀ ለ81 ዓመታት ዘልቋል፡፡

የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር በዓል ላለፉት 77 ያክል ዓመታት ያለምንም የመንግሥት ድጋፍ ወረዳዎች በየዓመቱ በየተራ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲያከብሩት መቆየቱን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ዘውዲቱ ወርቁ ተናግረዋል፡፡

ከ33 በማይበልጡ አባላት እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር በአሁኑ ወቅት ከ53 ሺህ በላይ አባላትን በማቀፍ የብሔረሰቡን ባህልና ወግ እያስተዋወቀ ነው፡፡

ዘንድሮ ለ81ኛ ጊዜ የሚከበረውን ይህ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በፈረስ ትርዒት፣ በፓናል ውይይቶችና በእደ ጥበባት ኤግዚቢሽን ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁንም አብመድ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.