Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን መንግስት ከተቃዋሚወች ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን መንግስት ከተቃዋሚዎች ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ ከሰሜኑ የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ (ኤስ ፒ ኤል ኤም፤ ኤን) ጋር የተፈረመ ነው ተብሏል።

የአሁኑ ስምምነት በቀጠናው የተያዘው የሰላም እቅድ አካል መሆኑም ነው የተነገረው።

ቡድኑ ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ በትጥቅ ትግል ላይ ቆይቷል።

ኤስ ፒ ኤል ኤም፤ ኤን የብሉ ናይል እና ደቡብ ኮርዶፋ አካባቢዎችን የማስተዳደር እቅድ እንዳለው ይነገራል።

ምንጭ ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.