Fana: At a Speed of Life!

የሲኖቫክ ክትባት በህፃናት እና ወጣቶች ላይ ውጤታማ መሆኑን ጥናት አመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይናው ሲኖቫክ ባዮ ቴክ የተመረተው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት በህፃናት እና ወጣቶች ላይ ውጤታማ መሆኑን ዘ ላንሴንት የተሰኘው የሜዲካል ጆርናል ጥናት አመላከተ፡፡

ከክትባቱ ውጤታማነት ባሻገርም የጎንዮሽ ችግር እንደማያስከትልም ነው ጥናቱ ያመላከተው፡፡

ጥናቱ እድሜያቸው ከ3 እስከ 17 ዓመት የእድሜ ክልል በሚገኙ ህፃናትና ታዳጊዎች ላይ የተሞከረ ነው፡፡

ህጻናቱና ታዳጊዎቹ ክትባቱን በ28 ቀናት ልዩነት ሁለት ጊዜ እንዲወስዱ ተደርጓልም ነው የተባለው፡፡

በጥናቱ ከ500 በላይ ጤናማ ህፃናትና ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ከ96 በመቶ በላይ የሚሆኑት ቫይረሱን የመከላከል አቅም አጎልብተው ታይተዋል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.