Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የአስፈጻሚዎች ስልጠና እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የአስፈጻሚዎች ስልጠና እየተካሄደ ነው።

እስከ መጭው ሃሙስ ድረስ በሚቆየው ስልጠና ከ5 ሺህ በላይ ሰልጣኞች ይሳተፋሉ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባል ወይዘሪት ብዙወርቅ ከተተ፥ ስልጠናው በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

ለህዝበ ውሳኔው የሚያስፈልጉ የህግ ማዕቀፎች፣ የመራጮች የምዝገባ ሂደት፣ የህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ፣ ቆጠራ እና ውጤት አገላለጽ እንዲሁም የህዝበ ውሳኔው ውጤት መገለጹን ተከትሎ የሚነሱ ቅሬታዎች የሚፈቱበት መንገድ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ብለዋል።

ሰልጣኞቹም ህዝበ ውሳኔው ተዓማኒ፣ ገለልተኛ እና ከተፅዕኖ የፀዳ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ስልጠናው ሰልጣኞች በህዝበ ውሳኔው ምዝገባና የምርጫ ሂደት በቂ ግንዛቤ እንዲይዙና ህዝበ ውሳኔዉን በገለልተኝነት ማስፈጸም እንዲችሉ ለማድረግ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

የህዝበ ውሳኔው ድምጽ መስጫ ቀንም ወደ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም መዛወሩንም ቦርዱ አስታውቋል።

 

 

በፋሲካው ታደሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.