Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ሁለተኛ ዙር የልዩ ሀይል አባላትን ለአገራዊ ጥሪ ሊልክ ተዘጋጅቷል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ሁለተኛ ዙር የልዩ ሀይል አባላትን ለአገራዊ ጥሪ ለመላክ መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
ልዩ ሀይሉ የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ እየሰራ መሆኑንና አገራዊ ጥሪን በመቀበለም ለአገር እድገት ነቀርሳ የሆነውን የህወሐት አጥፊ ቡድን ለማስወገድ ቆርጠው ተነስተዋል ነው ያለው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ፡፡
ህውሐት በፊትም ለህዝብ መለወጥና አንድነት ደንታ የሌለዉ ቡድን በመሆኑ የህዝቦችን አነድነት ለማረጋገጥና ቡድኑን እንዲወገድ ልዩ ሀይሉ የሚተጋ መሆኑን ነዉ ኮሚሺኑ የገለጸው፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና የገጽታ ግንባታ ዳሬክተር ኮማንደር መስፍን ዴቢሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ልዩ ሀይሉ የአገራዊ ጥሪዉን በመቀበል በወኔ እየተንቀሳቀሰ ነዉ፡፡
ጥሪዉን በማክበር ለአገሪቷ አንድነት የሚሰሩት የልዩ ሀይል አባላቱ ዛሬ 10፡00 ላይ በሀዋሳ ሽኝት እንደሚደረግላቸውም ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ ተናግረዋል፡፡
በጌታቸዉ ሙለታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.