Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አሰባሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ይፋዊ የመንግስት ምስረታ ሥነ-ስርአት በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የሲዳማ ክልል ይፋዊ የመንግስት ምስረታ ሥነ-ስርአት የፌዴራል እና የክልል የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተካሄደው፡፡
ዛሬ ይፋዊ የክልል መንግስት ምስረታውን ያካሄደው ክልሉ ከተለያዩ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ከ206.5 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማሰባሰብ ችሏል፡፡
የኦሮሚያ ክልል 100 ሚሊዮን ብር፤ የአማራ ክልል 30 ሚሊዮን ብር፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 50 ሚሊዮን ብር፤ የሶማሌ ክልል 10 ሚሊዮን፣ የሀረሪ ክልል 5 ሚሊዮን፣ የአፋር ክልል 7 ሚሊዮን እንዲሁም የጋምቤላ ክልል የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
የአርሲ ዞን 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፤ የሻሸመኔ ከተማ የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.