Fana: At a Speed of Life!

የሳይበር ደኅንነት ምርምር ለማካሄድ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የሳይበር ደኅንነትን ለማስጠበቅ የሚያስችል ምርምር ለማካሄድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር እና ስምንት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱ ፊርማ ብቻ ሳይሆን ወደፊት የሀገርን የሳይበር ደኅንነት በማስጠበቅ እንዲሁም ትውልዱን በዘርፉ ለመቅረፅ ለመሥራት እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡
ስምምነቱ÷ በሀገር ጉዳይ ላይ የሚፈጠሩ የሳይበር ደኅንነት ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እንደሚያግዝም ተመላክቷል፡፡

የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ እና የዩኒቨርሲቲዎቹ የሥራ ኃላፊዎች ናቸው ስምምነቱን የተፈራረሙት፡፡

ስምምነቱን የተፈራረሙት ዩኒቨርሲቲዎችም÷ ጎንደር፣ ሀዋሳ፣ አርባምንጭ፣ ባሕርዳር፣ ሐረማያ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የመከላከያ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ስምምነቱ በአቅም ግንባታና ተሰጥኦ ልማት ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.