Fana: At a Speed of Life!

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ በዘርፉ ጠንካራ ሀገራዊ አቅም መፍጠር የቻለ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በፖሊሲው አፈፃፀም ዙሪያ መክረዋል።
በምክክሩ አለም አቀፍ ትስስር በመፍጠር ሀገራዊ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ የሰው ሀብትንና መረጃን በማልማት፣ ዘመናዊ የፋይናንስ ማበረታቻ ስርአትን በመፍጠር መደላድል መሆን የቻለ ፖሊሲ እንደሆነም ማሳያ የሚሆኑ ተቋማት ተፈጥረዋል ተብሏል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን ሙሀመድ አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር የሚችል ትውልድ መፍጠር፣ ምርትና ምርታማነትን የሚያጠናክር አሰራሮችን ማበረታታት፣ እሴት ጨምሮ ወደ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ላይ በቅንጅት መስራት እና በአለም አቀፍ ደረጃ በየዘርፉ ተወዳዳሪ በመሆን መስራት በቀጣይ የቤት ስራ የሚሆኑ ጉዳዮች እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
በፖሊሲው የተቀመጡ አቅጣጫዎች ተግባራዊ ሲሆኑ ውጤታማ የምርምርና የአገልግሎት ዘርፍ ተቋማትን በመፍጠር ተጨባጭ ለውጦችን ማየት እንደተቻለም በተካሄደው መድረክ ላይ መነሳቱን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.