Fana: At a Speed of Life!

የሴቶችን መብት የሚያከብር ማህበረሰብ እንገባ በሚል 45ኛው ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የሴቶችን መብት የሚያከብር ማህበረሰብ እንገባ” በሚል መሪ ቃል 45ኛው ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ወሩን ሙሉ መከበር ጀምሯል።

የወሩ መጀመሪያ ሳምንት የሴቶች አመራርና ውሳኔ ሰጭነት ላይ ባተኮሩ የፖናል ውይይቶች እንደሚታሰብ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሙና አህመድ ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለት በሴቶች አመራርና ውሳኔ ሰጭነት ላይ የተደረገ ጥናት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የስርዓተ ፆታ ዳሰሳን የተመለከቱ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት ሚኒስትር ዲኤታዋ ሴት አመራሮችን ለመፍጠር ውሳኔ ሰጭነታቸውን ስኬታማ ለማድረግ በህግ የተደገፉ ስራዎችን ለመስራት እየተሞከረ ቢሆንም ከሴቶች ቁጥር አንፃር ውጤታማ አይደለም ብለዋል።

“በመሆኑም ነገ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የፖርቲ ሊቀመንበር ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ የምንፈልጋቸውን ሴቶች ዛሬ ላይ ልናዘጋጃቸው ይገባልምዕ ነው ያሉት።

45ኛው ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ማርች 8 የሴቶች ወር በቀጣይ ሶስት ሳምንታት የታዳጊ ሴቶች ትምህርትና የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት፣ ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት እና ፆታዊ ጥቃትን መከላከል በሚሉ ጉዳዮች በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይታሰባል፡፡

በመታገስ አየልኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.