Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች እና ህፃናት መብት እንዲከበር በአጋርነት እንደሚሰራ ዩኒሴፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች እና ህፃናት መብት እንዲከበር በአጋርነት እንደሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ህጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ አስታወቀ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከድርጅቱ ጋር በሴቶች እና ህፃናት ዙሪያ የሚከናወኑ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋየ ፥ በዚህ ወቅት ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ ሴቶች እና ህፃናት እንዲሁም በማህበራዊ ጉዳይ ላይ አያከናወነ ስላለው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በሀገሪቱ በተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ አደጋዎች ለሚከሰቱ ማህበራዊ ችግሮች ሲሰጥ የነበረዉን ምላሽ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል ሚኒስትሯ ጠይቀዋል፡፡

በተለይ ድርቅና ግጭቶች ያገጠሙባቸዉ አካባቢዎች ሰብዓዊ ቀውስ እንዳይባባስ፣ ያለዕድሜ ገብቻ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶች እንዳይከሰቱ ማህበራዊ ደህንነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በኢትየጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ጂያን ፍራንኮ ሮቲጂሊያኖ በበኩላቸው ፥ አጠቃላይ ለህጻናትና ሴቶች ደህንነት፣ መብትና ተሳትፎ መጎልበት እንደከዚህ በፊቱ ከተቋሙ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች የሚያስከትሉት ጉዳትና ጥለዉ የሚያልፉት ጠባሳ ቀላል አይደለም ያሉት ጂያን ፍራንኮ ፥ ይህንን እና ተጓዳኝ ችግሮችን ለማስወገድ ድርጅታቸው በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

በቀጣይ የሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም ግንባታበተመለከተ፤ የህጻናት ከገጠር ወደ ከተማ ፍልሰትና ጉልበት ብዝበዛን ለመከላከል ፤ያለዕድሜ ጋብቻን እና በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለማስወገድ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ከስምምነት መደረሱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.