Fana: At a Speed of Life!

የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ከድሬዳዋ አስተዳደር ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ከድሬዳዋ አስተዳደር ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ኤጀንሲ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ምክክር አካሂዷል።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የፌዴራል ስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ÷የከተማ አስዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲ አደረጃጀቱን የማሻሻል ስራ በማከናወን የተሻለ የስራ ዕድል ፈጠራን የማመቻቸት ስራ ማከናወን አለበት ብለዋል።

በዚሁ ወቅት ከተማ አስተዳደሩ በ2013 በጀት አመት ከ23 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

በባለፈው ዓመት ወደ ድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ይገቡ የነበሩ የተለያዩ ኩባንያዎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መዘግየታቸው የተጠቀሰ ሲሆን÷ በበጀት አመቱ  ግን በርካታ ኩባንያዎች ወደ በኢንዱስትሪ  ፓርኩ ይገባሉ ተብሏል።

በመሆኑም ከኢንዱስትሪ ፓርኩ እስከ 10 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች በቀጥታ የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑም ተመላክቷል።

ከዚያም ባለፈ ለኩባንያዎቹ የተለያዩ ግብዓቶችን በማቅረብ እና አገልግሎቶችን የሚሰጡ የተለያዩ የስራ መስኮችን በመፍጠር የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

በምክክሩ ላይ ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ጨምሮ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከዲር ጁሃር እንዲሁም በአስተዳደሩ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች መገኘታቸውን ከከተማው አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.