Fana: At a Speed of Life!

የስኳር ህመም

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአለም ላይ 422ሚሊየን አዋቂ ሰዎች የስኳር ህመም ተጠቂዎች ናቸው፡፡

ይህም ከ 11 ሰዎች አንድ ሰው የስኳር ህመም አለበት እንደማለት ነው።

ዋና ዋናዎቹ የስኳር ህመም አይነቶች ሶስት ሲሆኑ÷ Type 1 Diabetes ( አንደኛው አይነት የስኳር ህመም ) ኢንሱሊን የሚባለው ሆርሞን አለመመረት፣ Type 2 Diabetes ( ሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም ) የተመረተውን ኢንሱሊን ሰውነታችን መጠቀም ሳይችል ሲቀር ( Insulin resistance )፣ Gestational Diabetes ( በእርግዝና ጊዜ የሚመጣ የስኳር ህመም ) ናቸው፡፡

በአለም ላይ በየአመቱ 1ነጥብ5 ሚሊየን ሰዎች በስኳር ህመም ህይወታቸው ያልፋል፡፡

የስኳር ህመም የሚያስከትላቸው ችግሮችም የአንጎል ምት ( stroke )፣ አይነ ስውርነት፣ የልብ መድከም፣ የኩላሊት መድከም ፣ የእግር መቆረጥእና የቁስል ቶሎ አለመዳን ይጠቀሳሉ፡፡

በቤተሰብ ውስጥ የስኳር ህመም መኖር ፣ ዘረመል ፣ የእድሜ መጨመር በስኳር የመያዝ እድላችን የሚጨምሩ ቢሆንም አንዳንድ የአኗኗር ሁኔታዎች ለሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም ተጋላጭነትን ይጨምራሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ጤነኛ ያልሆነ የአመጋገብ ስርአት (የተቀነባበሩ ምግቦችን ማብዛት)እና አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ ሌሎች አጋላጭ ምክንያቶች ናቸው፡፡

ማድረግ ያሉብን እርምጃዎች ደግሞ ጤነኛ አመጋገብ መከተል፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ከልክ ያለፈ ውፍረት ማስወገድ፣ የሚጠራጠሩ ከሆነ የስኳር መጠንን መለካት እና የህክምና ምክሮችን መከታተል እንደሚገባ ከደቡብ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.