Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ፋርማጆ በኤርትራ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው እለት አስመራ ሲገቡ፥ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በአስመራ ቆይታቸው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከኤርትራው አቻቸው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ጉዳዮች እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ሀገራቱ ባሳለፍነው ዓመት ሀምሌ ወር ላይ የወዳጅነት እና የትብብር ስምምነት ከተፈራሙ በኋላ የኤርትራ እና የሶማሊያ ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን መሪዎቹ በውይይታቸው ወቅት ገልፀዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ የፈረሙት የሶስትዮች የትብብር ስምምነት አተገባበርም በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል።

በቀጣይም በደህንነት ወይም መከላከያ፣ በኢኮኖሚ እና በመሰረተ ልማት ዘርፎች በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.