Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው የህይወትና የአካል ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለፀ።

ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ለፍቶ አዳሪ ንጹሃን ዜጎችን በማጥቃት ሀገርንና ህዝብን ወደ ትርምስ ለማስገባት ተቀናጅተው የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶ የዜጎች ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ የክልሉ መንግሥተ የሚታገል መሆኑን ይገልፃል፡፡

የክልሉ መንግስት የፌደራል መንግስት በአጥፊዎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ህብረተሰቡም አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ እያቀረበ ሕይወታቸውን ላጡት ለቤተሰቦችና የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.