Fana: At a Speed of Life!

የሶስትዮሽ ድርድሩ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና መብት ባስከበረ መልኩ ይካሄዳል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ነገ ከሰዓት ቀጠሮ በተያዘለት በህዳሴ ግድብ ላይ የሚያተኩረው የሦስትዮሽ ድርድር የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና መብት ባስከበረ መልኩ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ድርድሩ ላይ የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የውሃ ጉዳይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።

የድርድሩ ሂደት የሶስቱ ሃገራት መሪዎች ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት የሚካሄድ መሆኑንም ቃልአቀባዩ ገልጸዋል።

ድርድሩ ስኬታማ እንዲሆን ኢትዮጵያ ፅኑ ፍላጎት እንዳላት መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ድርድሩ ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከተካሄደው የበይነ መረብ ውይይት በኋላ የተቋረጠ ሲሆን መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚቀጥል ቢገለጽም እስካሁን ሳይካሄድ ቆይቷል።

የግድቡ የሶስትዮሽ ድርድር የተቋረጠው በሱዳንና በግብጽ ምክንያት እንደሆነ ኢትዮጵያ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።

በህዳሴ ግድብ ላይ ያተኮረው የሶስትዮሽ ድርድር የተጀመረው ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.